Description
Birhan Gospel believers church is an evangelical christian church dedicated to reach Ethiopians & Eritirians living in Ireland with the gospel of the Lord.
Tell your friends
RECENT FACEBOOK POSTS
facebook.comChurch Teachings - Google Drive
Dear all, please find Sunday teachings following this link. Let me know if you are not included in this list. https://drive.google.com/drive/folders/0B0GFl2iHFjv4NkQxZTNiUWc5eUk?usp=sharing
Church Teachings
Church Teachings from July & August. https://drive.google.com/open?id=0B0GFl2iHFjv4NkQxZTNiUWc5eUk
Special Women program at Birhan Gospel Believers Church Dublin-Ireland
We have prepared a special program for all women in the church, Please come for the prayer section from 11:00 to 2:00 pm and for the Training session from 3:00-6:00pm
በማርቆስ ፈጣን ባቡር ውስጥ ይቅር ባዩ በዚህ አለ ማርቆስ 1: 40 – 2:17 ጌታ ኢየሱስ በምድር ላይ አገልግሎት የጀመረበት ዘመን ወንጌላዊው ማርቆስ እንደሚያሳየን ሰው በተለያየ እስራትና ቀንበር ውስጥ የነበረበት ጊዜ ነበር። በሮም አገዛዝ ምክንያት የነበረው የፖለቲካና የኢኮኖሚ ቀንበር እንዳለ ሆኖ የመንፈሳዊው እስራት ግን ከዛም የባሰ ዘመኑን አጨልሞት ነበር። ጌታም የእግዚአብሄር መንግስት ቀርባለች እያለ በታላቅ ስልጣን መፈታትን እያወጀና በተግባር ብዙዎችን ነጻ እያወጣ በገሊላ ዙሪያ ሁሉ ይመላለስ ጀመር። በዚህም ክፍል ነጻ አውጭው ይቅር ባይ ጌታ ሰዎችን ከሃጢያት እስራት ሲፈታ እናገኘዋለን። ለዘመናት ከሰው ተነጥሎ በሙሴ ህግ መሰረት ከከተማው ውጭ ለምጻም ተብሎ የተጣለውን በእጁ ዳሶ ቀድሶና አንጽቶ ከሰው ይቀላቅላል። በጉዋደኞቹ ብርቱ እምነት በጣራ አድርጎ ከናልጋው በዛ ቤት በጌታ እግር ስር የተዘረጋውን ያን ሽባ ሰው መጀመሪያ ከዋናው የሃጢያት እስራቱ ፈቶ የመንግስቱ ተካፋይ ካደረገው በሁዋላ አልጋውን አሸክሞ ሙሉ ሰው አርጎ ይሰዳል። መንገድ ዳር ያገኘውንም ቀራጭ አዲስ ሰው አድርጎ ለመንግስቱ ስራ ሊሾመው ጠርቶ ያስክትላል። በቤቱም ገብቶ ዘመኑ ከገፋቸው ሃይማኖተኞቹም ርኩስ ብለው ካገለሉዋቸው ጋር እየበላና እየጠጣስ ለወቃሾቹ ለነዚህ ነው የመጣሁት ብሎ መልስ ይሰጣል። ማርቆስ ሃጢያትን የሚያስተሰርይ ነጻ አውጪው የእግዚአብሄር ልጅ በዚህ አለ ይለናል። እሱ ታዲያ ዛሬም ሰዎችን ከሃጢያት ባርነት ነጻ ሊያወጣ በዚህ አለ።
Church Teachings
https://drive.google.com/open?id=0B0GFl2iHFjv4NkQxZTNiUWc5eUk
Birhan Gospel Believers Church Dublin-Ireland
Birhan Gospel Believers Church Dublin-Ireland
ኑ ቡና ጠጡ!
የቅዳሜ ከሰአት በሁዋላን ከኛ ጋር እየተጫወቱ እንዲያሳልፉ ከቤተሰብዎ ጋር በአክብሮት ተጋብዘዋል። ፕሮፌሰር ዩሃንስ ይግዛውከሰላሳ አመት በላይ የአየርላንድ ቆይታቸውን ያጫውቱናል እንዲሁም ለልጆች የሚሆን ልዩ ዝግጅትም ተሰናድቱዋል። ይምጡና ድግሳችንን ይታደሙልን።
Come and attend this series on the Gospel according to Mark. በማርቆስ ፈጣን ባቡር ውስጥ -part 2 Summary. የበረሃው ዝግጅት ማርቆስ 1: 1-13 የማርቆስ ፈጣን ባቡር ገና ከመነሻው ይዞን የሚሄደው ወደ በረሃ ነው። በረሃ ወይም ምድረበዳ በመጽሃፍ ቅዱስ ውስጥ እግዚአብሄር ሃሳቡን ለልጆቹ የሚገልጥበት ሁነኛ ስፍራ እንደሆነ በብሉይ የተጻፈው የእስራኤል ታሪክ ያሳየናል። በዚህም ክፍል እግዚአብሄር አዲሱን ኪዳኑን በኢያሱስ በኩል ሲገልጥ መነሻው በበረሃ እንደሆነ ማርቆስ ይነግረናል።በዚህ በራሃ የሚጮህ የምንገድ ጠራጊው የመጥምቁ ዩሃንስ ድምጽ አለ። ከኢየሩሳሌም ወደ በረሃ ውጡና ንስሃ ግቡ እያለ ህዝቡን ባዶ ሃይማኖተኝነትን ትተው በበረሃ ወደ እግዚአብሄር እንዲመለሱ ይጋብዛል። በዚህ በረሃ ሃጢያት የሌለበት ቅዱሱ የእግዚአብሄር ልጅ ጽድቅን ይፋጽም ዘንድ ተጠመቀ። ሰማያትም ተቀድደው አብ ስለልጁ መሰከረ መንፍስ ቅዱስም ዳግም ፍጥረትን ሊያውጅ ከላይ ወረደ። ኢየሱስንም የዚህን አለም የጨለማ ገዢ ይፋለም ዘንድ ለአርባ ቀን ወደበረሃ ወሰደው። ዛሬም በህይወታችን የምናልፍበት በረሃ ቢኖር አንድም ሊያጠራንና ወደ አባታችን ሊመልሰን ሲሆን አልያም ለክብሩ ወንጌል አገልግሎት ሊያዘጋጀን ነው።
Come and attend this series on the Gospel according to Mark. በማርቆስ ፈጣን ባቡር ውስጥ ማርቆስ 1:1 - መቅድመ ዘማርቆስ ቅዱስ ማርቆስ የጻፈለን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ልክ እልፍ ፉርጎዎች እንዳሉት ፈጣን ባቡር ነው። በዚህ ወንጌል 16 ምዕራፎች ውስጥ ጌታ ኢየሱስን የምናገኘው በገሊላ ክልልና ኋላም በኢየሩሳሌም በጉዞ ላይ ሲሆን ታረኩም ወዲያው ወዲያው የሚከናወን በፍጥነት የተሞላ ነው። በመጀመሪያው ቁጥር ላይ የምናነበው የዚህ ውንጌል ንዑስ ርዕስ ማርቆስ ለነዛ በሮም ግዛት በስደትና በመከራ ላሉ ክርስቲያኖች ሊያስተላልፍ የፈለገውን መልእክት ፍንትው አርጎ ያሳያል። የዚህ የድል ብስራት ወንጌል መጀመረያ የኢየሱስ ክርስቶስ ምድራዊ አገልግሎት እንዲሁም ሞቱና ትንሳኤው ሲሆን ተረካቢ ባለአደራዎቹም እነዛ ግራ የተጋቡና በፍርሃት የተያዙ ደቀ መዛሙርት ናቸው። ታድያ በማርቆስ 16 ምዕራፎች ውስጥ የምናየው የዚህ የማይቆም ወንጌል ጅማሮ ላለፉት 2000 አመታት “ሲያጠፉት እየነደደ ሲያፍኑት እየባሰ” እኛጋ ደርሷል። እኛም እንደቀጣይ ባለአደራዎች ዛሬም አለምን ሁሉ ሊያድን የተገለጠውን የእግዚአብሔር ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል እንሰብካለን።
According to the will of the Lord, our Annual Peniel program will be held from August 18 to August 21 in Castledaly Manor Athlon. Those of you who haven't yet put it in your calendar and get prepared.
Let's invite others to like this page so that they can get all the events and programs we organize.
Quiz
